ፓርክላንድ ኮሌጅ አርባምንጭ በዲግሪ ፕሮግራም ሙሉ እውቅና አገኘ

9 September 2023

ፓርክላንድ ኮሌጅ አርባምንጭ በጤናና ቢዝነስ መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ ሙሉ እውቅና ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርትና ባለስልጣን አገኘ።

በዚህም የኮሌጁ የአስተዳደር ሰራተኞች እና መምህራን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የኮሌጁ ፕሬዚደንት እና ባለቤት የሆኑት ቴዎድሮስ ፋንታዬ (እጩ ዶ/ር) በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ “በመጀመሪያም ይህ እንዲሆን የረዳኝን ልዑል እግዚአብሔርን እና በምልጃቸው ያልተለዩኝን ቅድስት ድንግል ማሪያምን፣ ቅዱሳን መላእክትንና ፃድቃን ሰማእታትን እያመሰገንኩና እያከበርኩ በዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ ከጎኔ ያልተለያችሁ ቤተሰቦቼ ፣ ውድ ጓደኞቼ እና ለኮሌጁ ማህበረሰብ ላቅ ያለ ምስጋና ላቀርብ እወዳለሁ” ብለዋል።