ፓርክላንድ ኮሌጅ ለጋሞ ዞን ፖሊስ አባላት ለ2ኛ ዙር መሰረታዊ የኮምፒውተር ክህሎት ስልጠና ሰጠ
23 July 2022
ፓርክላንድ ኮሌጅ አርባምንጭ ካነገባቸው አላማዎች አንዱ የማህረሰብ አቀፍ አገልግሎት ሲሆን ይህንንም አገልግሎት ለተለያዩ የህብረተሰብ
ክፍሎች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጀቶችን ተደራሽ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል።ከነዚህም የማህበረሰብ አገልግሎቶች መካከል
በዛሬው እለት ከጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ለተውጣጡ ባለሞያዎች መሰረታዊ የኮምፒውተር ክህሎት ስልጠና በመስጠት ስልጠናውን
ለተሳተፉ አባላት የመምሪያው ሀላፊዎችና እና የኮሌጁ ዲን አቶ መንግስቱ እና መምህራን በተገኙበት ተበርክቶላቸዋል።
የኮሌጁ ፕሬዚዳንት ስልጠናው የተሳካ እንዲሆን አስተዋፅኦ ላበረከቱ መምህራን አባይነህ እና መብራቱ በፓርክላንድ ኮሌጅ እና
በኮሌጁ ማህበረሰብ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።







