ፓርክላንድ ኮሌጅ የተማሪዎችን ቀን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ
27 August 2022
በፓርክላንድ ኮሌጅ በአመት አንዴ የሚከበረው የ2014 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ቀን በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል። በፕሮግራሙም ላይ የኮሌጁ ሰራተኞች፣ መምህራን፣ ተማሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ይህ በኮሌጁና በተማሪዎች መማክርት ቅንጅት የተዘጋጀው መርሃ ግብረ የተለያዩ የመዝናኛና ቁምነገር አዘል ዝግጅትም ነበር። የኮሌጁን ዲን አቶ መንግስቱ ጥላሁንን ጨምሮ የኮሌጁ አመራሮች ስለመማር ማስተማር፣ የተማሪዎች መብትና ግዴታ በተመለከተ አጭርገለፃ ያደረጉ ሲሆን ፕሮግራሙም ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ሽልማት በመስጠት የኢትዮጵያን ህዝብ ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር ተጠናቋል።







