ለጋሞ ዞን ፖሊስ አባላትና አመራሮች ለሁለተኛ ዙር በስራ አመራር እና ህዝብ ግንኘት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ

7 February 2023

ፓርክላንድ ኮሌጅ አርባምንጭ ካነገባቸው አላማዎች አንዱ የማህረሰብ አቀፍ አገልግሎት ሲሆን ይህንንም አገልግሎት ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጀቶችን ተደራሽ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል። ከነዚህም የማህበረሰብ አገልግሎቶች መካከል በዛሬው እለት ከጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ለተውጣጡ ባለሞያዎችና አመራሮች በስራ አመራር እና ህዝብ ግንኘት ክህሎት ስልጠና በመስጠት ስልጠናውን ለተሳተፉ አባላት የመምሪያው ሀላፊዎችና እና የኮሌጁ ዲን አቶ መንግስቱ እና መምህራን በተገኙበት ተበርክቶላቸዋል። በጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያም ለኮሌጁ የምስክር ወረቀት ተበርክቷል።